GGMNOLFNKFHJFMJHNOH

Iklan

iklan

Iklan

iklan

Entertainment

Video View All

Powered by Blogger.

Search This Blog

Economy

Sport

Health

Music

Comments

Advertisement

Iklan

iklan

መልህክትሽ እንደወረደ ..... ሃሳብሽን ኩልል አርገሽ መግለፅ ስለምትችይ ..... ከኮመንት ቦታ በጣም ፊለፊት መሆን ስላለበት

Eriyot Alemu
November 27, 2025 Last Updated 2025-11-27T21:47:59Z



በአካል አንድ ቀን ካየሁህ ውጪ በፌስቡክ ነበር የማውቅህ። ኮሜርስ አካባቢ ያለ መጠጥ ቤት ያዘወትራል ላሳይሽ ብሎ ሲያመጣኝ ጥርስህ እንደዛ አብጦ አልኮል ትጠጣ ነበር። ከዛ ከኪስህ የጥርስ መዳኒት አውጥተህ በአልኮል ስትወስድ አጠገብህ ነበርኩ። ሱሰኛ መሆንህ እስኪበቃኝ ተነግሮኝ ነበር። በአካል ያየሁህም ቀን በጣም ጠጥተህ ነበር። ግን ሳቅህ አወራርህ ድምፅህ መጠጡን አስረስቶኝ ነበር። ብቻ ሱስህን የምታገለው መስሎኝ ነበር። እጅግ ሲበዛ አፍቅሬህ ነበር። ግን ይሄ መዳኒት በአልኮል መውሰድ ፈተነኝ። ተኝቼም ስነሳም ይሄ ሲን ከአይኔ አልጠፋም አለኝ። አሁንም ትዝ ይለኛል። እንደዛም ሆኖ ተስፋ አልቆረጥኩም። ያን ቀን እህቴም አብራኝ ነበረች። ከመጠጥ ቤቱ ስትወጣ ተከተልንህ ከናዝሬት ፔንሲዮን አጠገብ በድጋሚ ጫት ስትገዛ አየሁህ። ከሰዓት ሙሉ ስትቅም እንደነበር አውቄ ነበር። መጠጥ ቤት የጠበቅንህ ቅመህ ጨርሰህ እስክትመጣ ነበር።  በድጋሚ ጫት መግዛቱ እኔን አደነዘዘኝ። ጫቱን ኪስህ ከተህ ወደቤትህ አቅጣጫ ታክሲ እስክትይዝ ድረስ ብንከተልህም እጅግ ደንዝዤ ነበር። ያየሁት ከሰማሁትም ከአዕምሮዬም በላይ ሆነብኝ። እህቴና ጓደኞቼ ከዚ በዋላ ካላበድሽ በቀር ይሄን ልጅ ስሙን እንዳጠሪው አሉኝ። ታግያለሁ ግን ተስማማው። ታምሜ ታምሜ ቆይቶ ቆይቶ ፍቅርህ ወጣልኝ መሰለኝ። ብዙ ብዙ አልቅሻለው። ብዙ ብዙ ሆኛለው። እንደጥፋትህ ፌስቡክ ላይ ብሎክ ሳደርግህ እህቴ ጀግና ብላ ግምባሬን ሳመቺኝ። በሞት እንደተለየሁህ ነው ያለቀስኩት። ከዛ በዋላ ለብዙ አመት ስላንተ ሰምቼም ደግሜም አይቼህም አላውቅም። በመሃል ሱሰኛ ስሸሽ ስሸሽ ቆይቼ፣ ወንድ ራሱ ስሸሽ ስሸሽ ቆይቼ ንፁህ ሰው አግኝቼ አፍቅሬ አገባው። እርግማን መሰለኝ ሁለት ወር አልቆየሁም ሱሰኛ መሆኑን ሳውቅ። ግን ባሌንም በጣም አፈቅረው ነበር። ያንተን ስህተት ላለመድገም ይመስለኛል በብዙ ልረዳው ሞከርኩ። አባስኩበት መሰለኝ እየሸሸኝ ሱስ ውስጥ የባሰ መዘፈቅ ጀመረ። እንደሚያፈቅረኝ አውቃለው ግን ይሸሸኝ ጀመር። አንዳንዴ ሲብስበት ስለ ሱስ አታውቂም ተይኝ ብሎ ይጮህብኛል። ታገልኩ ታገልኩ አቃተኝ እንደፈለገ ይሁን ብዬ ተውኩት። በተጋባን በአራት አመቱ ከአቅሜ በላይ ሆነና ተለያየን። በእድሌ እንጂ በማንም አላዘንኩም ነበር። ልጄን ይዤ ከሃገር ወጣው። በመሃል ልጅ ስላለ በስልክ እንገናኝ ነበር። አሁን ዘንድሮ ስመጣ በጣም ተለውጦ አገኘውት። በጣም ነው ደስ ያለኝ። የልጄ አባት ሱስ እርግፍ አድርጎ መተዉ እንዴት አያስደስተኝ። ግን በሱስ ዙሪያ ላናወራ የማልኩትን መሃላዬን ሽሬ ምን እንደለወጠው እንዲነግረኝ ጠየኩት። ታሪኩን ሳሳጥርልህ በመጀመሪያ ፀበል ተጠምቆ እግዜር እንደረዳው ነገረኝ። ከሆነ ጊዜ በኋላ ሱስ ላይ ከሚሰራ ሰው ጋር መገናኘቱ ሱስ ትቶ እንዲቆይ እንዳገዘው አስረዳኝ። እኔ ያልቻልኩትን የቻለ ሰው ማነው ስለው እሪዮት ይባላል ሲለኝ ኦልሞስት ወድቄያለው። ስረጋጋና በትክክል አንተ መሆንህን ሳረጋግጥ በጋብቻ እያለን ያልነገርኩትን የአንተን ታሪክ የነገርኩት። ዝም ነው ያለው ረዥም ጊዜ። በፊት ስላልነገርኩት ቅር እንዳለው ያስታውቅ ነበር። ቅር አላለኝም ለምን እንዳልነገርሺኝ ይገባኛል ቢለኝም ቅር እንዳለው ያስታውቅ ነበር። አንዳንዴ በህይወቴ ለምን እንዲህ እንደሚሆን ግራ ይገባኛል። በነገርህ ላይ በአንተም ህይወት ለውጥ በጣም በጣም ተደስቻለው። የባሌን ጉዳይ ከተለያዩ ሰዎች ቀድሜ ስለሰማው ለማመን አልተቸገርኩም ነበር። የአንተ ግን ምንም መረጃ ስለሌለኝ ለማመን ከብዶኝ ነበር። ዌብሳይትህን ነግሮኝ ስለነበር 10 ቀን ሙሉ እዚህ ሳነብህ ነበር። የኔ ነገር ማለቂያ የለውም። ቡክ ኦፍ ማይ ማዘር የሚለው ፅሁፍ ላይ ራሴን አገኘዋት። አንድ መስመር ብትሆንም እኔን ልታነሳ ባታስብም ጠቅሰኸኛል። ካልተሳሳትኩ ሱስ ለመተው መንገድ የጠረገው እኛ ቤት ያደርክበት አጋጣሚ ይመስለኛል። ያቺ ብቸኛ እኔን ካንተ ያስተዋወቀች ቀን ለአንተም ልዩ ቀን ነበረች ለካ። ያው ልዩ ቀንነቱ መልኩ ቢለያይም። ለአንተ ልዩ ቀን የሆነው በምሬት ነበር። ለኔ ደግሞ በደስታ። ለልጄ አባት ስነግረው ይሄማ እውነት አይመስልም ፊልም ነው አለኝ። ብቻ ህይወቴ እንቆቅልሽ ይሆንብኛል ብዙ ጊዜ። የቅርብ አብራቹ የተነሳቹትን ፎቶ አሳየኝ። ያለ ፀጉር በጣም ልጅ ሆንክብኝ። ለማመን ሁሉ ተቸግሬ ነበር። ብዙ ሰው እንደዛ ይለዋል ሲለኝ ነው አንተ ነህ ብዬ አምኜ የተቀበልኩት። እኛ አረጀን እኮ ከዋላ መጥተን። በጣም አምሮብሃል ደግሞ። በአካል አገናኝሻለው ብሎኝ ሁሉ ነበር ግን ጊዜ ቀደመኝ። ይሄን ታሪክ ከሀ እስከ ፐ ንገሪው ብሎ ያደፋፈረኝ የልጄ አባት ነው። ስትነግሪው ውስጥሽ ነፃ ይሆናል ይቀልሻል ብሎ አሳመነኝ።  ስለ ሱስ የፃፈው ስር ፃፊለት የሆነ ሰው ይማርበታል ብሎ ገፋፋኝ። ሁለታቹ በዚ ጉዳይ የምትግባቡ ይመስለኛል ቅር ከተሰኘህ ተወው። ደስ ካለህ ግን ራስህ ፃፍልኝ።  ስንት ቀን እንደፈጀብኝ ይሄን ለመፃፍ ግን አጠይቀኝ። መፃፍ ለካ እንዲህ ጭንቅ አለው። የልጄ አባት እዚህ ድረስ የፃፍኩትን ሳሳየው የሆነውንና ያለኝን ራሱ ይንገርህ። ብዙ ቀን እንደፈጀብኝ ይኸው ከአንተ እኩል ይስማ። አሁን በልጄ አባት የተነሳ ስሜን እንደምታውቀው አውቄያለው። ስለኔ ብዙ እንደሰማህም ነግሮኛል። በፌስቡክ ስሜ የምታስታውሰኝ አይመስለኝም። ያኔ በአካል ካስታወስካት ግን ስምህን አቀዋለሁ ያለችህ ሴት ነች ይሄን ሁሉ የፃፈችልህ። የልጄ አባት አዲስ ሰው በሆነበት መንገድ ውስጥ ስላለህ ምስጋናዬ በሱ በኩል ይደርስሃል። ሌላ ምን እንደምልህ አላውቅም። ትልቅ የተማርኩት ትምህርት ግን ሰው ካልሞተ በቀር ይለወጣል የሚለውን ነው። በህመም ውስጥ ይሄን ስላስተማራቹኝ ሁለታቹንም አመሰግናለው። ካላስቸገርኩህ ቅር ካለህ ዝምብለህ ተወው።  አንተ ላይ ምንም ካልፈጠረ ግን ለኔ ይጠቅመኛል የምር። ለምን ፊለፊት እንዲወጣ እንደፈለኩ አምላኬ ምስክሬ ነው ምክንያቱን አላውቅም። ብቻ ፊለፊት አርግልኝ። የልጄ አባት እውነቱን ነው አሁን የቀለለኝ ይመስለኛል። ተነፈስኩ።
Show comments
Hide comments