Komentar baru

Advertisement

የኛን ተሞክሮ!

Eriyot Alemu
Nov 25, 2025
Last Updated 2025-11-28T09:12:40Z
Advertisement

 



ጨረቃዋም ብርሀን የላት
ከጣ'ይቱ ላይ አንፀባርቃ
ብትታየን ከጠፈሩ
ከከዋክብት ጎልታ ደምቃ
የተውሶ ለተውሶ
አልናትና ለጨረቃ
የኛኑ ንድፍ በሷ ብርሀን
አሰናድተን ስናበቃ
ጨለማውን ተገን አርገን
በብርሀኗም ፍፁም አምነን
ምድርን ሳንለቅ
ምድርን ይዘን
ቤት ገነባን
ከቤታችን ራቅ ብለን። 


ታዲያ እኛ......
"የጨረቃ ቤት" ብለነው
ግብረ ብዙ ስም ብንሠጠው
ያለን ማስፋት እንጂ
መፍጠር የማይችሉት
የኛን ተሞክሮ
አስፍተው ለጠጡት::
የጨረቃ ቤት ስንል ስለሠሙ
ጨረቃ ላይ
ቤት ለመስራት አለሙ። 

iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

Leave Your Comment

Post a Comment

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement