Komentar baru

Advertisement

አልተገናኝቶም

Eriyot Alemu
Nov 25, 2025
Last Updated 2025-11-27T21:47:26Z
Advertisement

 





ቢወዳት!
እሷን እንዳያጣት!
ውስጡን አሳምኖ
አመሉን አርሞ
ፀጉሩን ተከርክሞ
ጀዝባነቱን ፆሞ
ይዘክራት ጀመር
ከቤተስኪያን ቆሞ። 

***************

ብትወደው!
ልክ እሱ እንዳረገው!
አመሏን ቀይራ
ራሷን ሞሽራ
ፀጉሯን አንጨባራ
እሱን እያሰበች
ወጣች ለጭፈራ። 

**************

ታዲያ እኚ ምስኪኖች...
አንድ ሁኑ ባይላቸው
ያኔ ሲፈጠሩ
አንዱ አንዱን በመሆን
ገብተው ሲዳክሩ
ማንም የማን ሳይሆን
ተለያይተው ቀሩ። 

iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

Leave Your Comment

Post a Comment

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement