Komentar baru

Advertisement

ምክር እና ምክር አሰማም ጥበብ አንድ

Eriyot Alemu
Nov 25, 2025
Last Updated 2025-11-26T19:21:15Z
Advertisement

 



"መካሪ ጠፍቶ ብቻ አይደለም ችግር ውስጥ የተዘፈቅነው፣ አንዳንዴ ምክር አሰማማችንም ላይ ችግር ስላለ ነው!" የሆነ ሰውዬ ሲል የሰማሁት።  

አንድ ባለትዳር ወዳጄ ደውሎ "ከባለቤቴ ጋር መስማማት አልቻልኩም፣ ምከረኝ" አለኝ።  በእውነት ክው አልኩ። ግን ማውራት አልተሳነኝምና "እንዴ እኔኮ ስመከር እንጂ ስመክር አይመቸኝም።  በዛ ላይ ወንደላጤ እኮ ነኝ!" አልኩት የሞት ሞቴን።  "እሱንማ አቃለሁ! ግን ቃልኪዳን መፅሄት ላይ 'ከባለትዳሮች ይልቅ ወንደላጤዎች የሴቶችን ባህሪ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ባያውቁ ኖሮማ ያገቡ ነበር' የሚል ነገር አንብቤ ነው:" አለኝ።  አባባሉ ባይዋጥልኝም እንደ መካሪ ወቅታዊ ሞቅታ ስለተሠማኝ ጉሮሮዬን ሞረድኩና "በል ማስታወሻ ያዝ!" አልኩት። 

 "ሴቶች በተፈጥሮአቸው፣ አገቡም አላገቡም መደነቅን ሁሌም ይፈልጉታል።  መስታወት ፊት የትየለሌ ሰዓት ተገትረው ቢያሳልፉ እንኳ ውበታቸውን ማረጋገጥ የሚፈልጉት በጆሯቸው ነው።  ሆኖም አድናቆትን ከብዙ ሰው ቢፈልጉትም፣ በተግባር ግን እንዲገልፅላቸው የሚፈልጉት፣ የግሌ የሚሉት አንድ ሰው ነው።  ስለዚህ ትዳርህን እንከን አልባ ለማረግ፣ ቋሚ አድናቆቶችን ሳታጓድል፣ ሌሎች በቃላት የሚገልፁላትን አንተ ደግሞ በተግባር አሳያት!" ብዬው በረጅሙ ተንፍሼ ስመለስ ስልኩ ተቋርጧል።  እፎይ አልኩ... ማታም ሆነ። 

መልሶ ደወለ....  "እህህ ምን ልበል?" አልኩት ቅድም ጆሮዬ ላይ ስለዘጋብኝ የተቀየምኩ እንዳይመስለው የድምፅ ፈገግታ እያሰማሁ።  በሰቅጣጭ በሆነ ድምፅ ማውራት ጀመረ... "ይኸውልህ ባለቤቴ ራት የሠራችው፣ በቅቤ ያበደ ፍርፍር ነበር።  እና ጐረቤቶቻችን ሸቷቸው ይሁን እግር ጥሏቸው ከች ከች አሉ።  ታዲያ ጥርግ አርገው ከበሉ በኋላ በአንድ ድምፅ 'ፍርፍርሽ ጣት ያስቆረጥማል!' አሏት" አለና ማቃሰቱን ቀጠለ።  የሣቄን ማፈኛ ነቅዬ ለመጀመሪያ ጊዜ በእብድ ሣኩ።  በቅቤ ባበደው ፍርፍር ማለቴ ነው።  ... ጀለስ ለካ ፍቅሩን ለባለቤቱ በተግባር ለማሳየት ብሎ፣ ጣቱን ቆርጥሞላት ነው።  ሆዴን እስኪያመኝ ድረስ መሣቄን ቀጥያለሁ ሃ ሃ ሃ... "ምን አሣቀህ?" አለኝ ከሱም ብሶ: "በል ሴቶች ደሞ ለነሱ ስትል የከፈልከውን መስዋትነት ቢያቁትም፣ ካንተ አፍ ሲሰሙት በፍፁም ደስ አይላቸውምና ሌላ ምክንያት ፈጥረህ ንገራት።  ታከብርሃለች!" ስለው ስልኩን በፍጥነት ዘጋው።  በገዛ እጄ አበሳዬን አሳየኝ።  

ሰዓት እላፊ ላይ መልሶ ደወለና... "ሠራ እኮ!" አለኝ።  "ምኑ? ጣትህ ነው?" አልኩት ለማለት ታክል።  "አረ ያልከኝ ነው" ብሎ የሚሠማ ሣቅ ሣቀልኝ።  "እንዴት ሆኖ ባክህ?" ቀጣዩን ለመስማት ቸኩያለው። 
 " 'ሌባ ጣትህ ምን ሆነ ፍቅሬ?' አለችኝ" ብሎ ጀመረልኝ።  "ምን አልካት ፍቅሯ?" ብዬ ማፍጠኛውን ተጫንኩት... "ይሄ ጣቴ የራሴን ጉድፍ ሳያወጣ፣ የሰው ጉድፍ ለማሳየት ፈጥኖ ስለሚቀሰር፣ ራሴ በራሴ ቀጣሁት" አልኳት።  
"ምን አለችህ ባያሌው?" 
"አንተ ትኮራብሃለች እንዳልከኝ....  'ኮራሁብህ' ብላ ግንባሬን ሳመችኝ!" ብሎ ዓይኑን ጨፈነ።  (ቪዲዮ ኮል ሆኖ ነው ዓይኑ የታየኝ ሃ ሃ ሃ) .... እንቅልፌ ስለመጣ ትንሽ አፋሸኩና "እንዲህ ነው እንጂ ወዳጄ! በል ደሞ ሴቶች ቀጣይነትን ስለሚሹ፣ ባለጌ ጣቴ በሰው ፊት እየጠነቆለ ባለጌ ስላሰኘኝ ትልና፣ እሱንም ትገምጥላታለህ... ያኔ ግንባርህን ሳይሆን ከንፈርህን ትስምሃለች ብዬ ጆሮው ላይ ጥርቅም አረኩበት። ቀድሞ ሳይዘጋው መቅደሜ ነው ሃሃሃ 

መካሪው ምን አጠፋ? እስቲ እንወያይበት 

iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

Leave Your Comment

Post a Comment

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement