Advertisement
ረዘም ላለ ጊዜ የጠፋነው ወደ ሌላኛው ገጽ ዞረን ስለነበር ነው። በአካልም እዚም። እነሆ እግዜር ፈቅዶ ምክንያታችን ይኸው ነው ለማለት በቃን። ገጹን ገፀ በረከት ይኸው!!!! ቀድመው የአዘጋጁን ማስታወሻ ያነቡት ዘንድ ማስፈንጠሪው ቀድሞ ወደዚያው ይወስዶታል። እዛው Home የሚለውን ተጭነው ይቆዩ ብለናል!!!! አልያም ቀጥሎ በተቀመጠው ማስፈንጠረያ ቀጥታ ወደ ዋናው ቤት ይሂዱ። እንደ ቤትዎ ይሰማዎ!!!!



እንዳንተ አይነት ከሌላ ሙያ ወደ ስነጽሑፍ የሚመጡ ሰዎች ሁሌም የሚጨምሩት ነገር አለ። ልክ እንዳንተ ኤሌክሪካል ኢንጂነር የሆኑት ፕሮፌሰር ግርማ ሙሊሳ ስነጽሑፉን አለም ከቴክኖሎጂ ጋር በጽሑፎቻቸው ሲያገናኙት ነበር። ሆኖም ዌብሳይቱ ላይ ብፈልጋቸውም ላገኛቸው አልቻልኩም። ከፈለክ ሁለት መጽሐፎቻቸው አሉኝ ላጋራህ እችላለሁ። በምን መልኩ ነው መረጃ የምትፈልገው?
ReplyDeleteየምትፈልገው ዓይነት ሰው ቤትህ ሲገኝ እንዴት ነው ዘላቂ ቤተኛ የምታረገው? በግ አርደህ ይሆንን? ፆመኛ አልያም አትክልተኛ ቢሆንስ? ትርፉ ኪሳራ ሊሆን ነው ኣ ሃሃሃሃ በቃ ቤተሰብ የምታረገውን ሰው ቤት ያፈራውን ነው የምትጋብዘው። መስማማትህን ጭንቅላትህን በመነቅነቅ መግለፅህን ስድስተኛ ስሜቴ ገልፆልኛል። ስለመጣህ እጅግ እጅግ በጣም አድርጌ አመሰግናለህ።
Deleteበአዲሱ ዌብሳይታችን ዙሪያ ቀደምት አስተያየት ሰጪዎች ውስጥ በመኖርህ ከ10 አመት በኋላም ብጠይቀኝ አረሳህም። አስር አመት ሳስፈርምህ አየህ አደል? ሃሃሃሃ ከመጽሐፍ ርቆ የማይርቀውን ሰው በፊደል አጣጣሉ ስለምለየው ነው ሃሃሃሃ
ስላስደሰትከኝ ነው መለፍለፌ… በምፈልገው መንገድ ስለመጣህ። ይሄን ካልኩ ዘንዳ ወደ ጥያቄህ ልሂድ። በመጀመሪያ “የአዘጋጁ ማስታወሻ” የሚለውን ያዘጋጀሁት ሰዎች ስለ ዌብሳይቱ ሙሉ ስዕሉ እንዲኖራቸው ነው። ገና ወደ ገፁ እንደገባህ አይን አዋጅ ሆኖብህ ማንበቡን ቀስ ብዬ ይደርሳል ብትል እረዳሃለሁ። ደግመህ አንብብልኝ ግን።
አንተ የገጠመህን አይነት ችግር ሰዎች ሊገጥማቸው ስለሚችል “የአዘጋጁ ማስታወሻ” ላይ አንድን ደራሲ የምንፈልግበትን መንገድ ግልፅ አድርጌ አስቀምጫለሁ። ወደ አንተ ምሳሌ ስንመጣ ፕሮፌሰር ግርማ ሙልኢሣን እናገኛለን። የጠፉብህ ሰርች ስታደርግ ግርማ ሙሊሳ ብለህ ስለፈለካቸው ነው። የሳቸው ስም ግን ግርማ ሙልኢሣ ነው። በዚ ስም ሰርች ብታረጋቸው ይመጡልህ ነበር።
ቋሚ ደንበኛ አድርጌ ስላስፈረምኩህ ከዚ በኋላ እንደዚህ አይነት ስሞች ሲገጥሙህ የአዘጋጁ ማስታወሻ ላይ እንደዘረዘርኩት የተለያዩ መፈለጊያ መንገዶችን ተከተል። ለምሳሌ ግርማ ብቻ ብለህ ብትጽፍ ሁሉም ግርማዎች ስለሚመጡልህ ከዛ ውስጥ መፈለግ ያን ያህል ከባድ አይሆንም። በእንግሊዝኛም Girma Mulisa ብለህ ብትጽፍ ነገር ታቀላለህ። አማርኛ ድርብ ሆሄሃት ስላሉት ጽሑፍ ላይ ለሰርች ጥንቃቄ ይፈልጋል። እዚሁ ምሳሌ ላይ ግርማ ሙልኢሣን ግርማ ሙልኢሳ ብለህ ብትፈልገው እንኳ አታገኘውም ነበር። ስዩም ሥዩም ወዘተርፈ ዓይነት ….ድርብ ሆሄሃት ያላቸው ላይ ለሌላ ጊዜ ጥንቃቄ እንድታረግ ነው። በአንዱ መጽሐፍ ስራቸውም ብትፈልጋቸው ታገኛቸው ነበር።
እናም በግርማ ሙልኢሣ ስም ግባና መረጃዎቹን ተመልከት። በስማቸው አራት መጻሕፍት አስገብቻለሁ። አንተ ጋር ያሉትን ሁለት መጻሕፍት ከነዚህ ጋር አመሳክረህ የሚጨመሩ ከሆኑ፣ የሚስተካከል ነገር ካለ፣ እዛው ዌብሳይት ላይ ባለው ቴሌግራም አድራሻ ልታገኘኝ ትችላለህ። መጽሐፉን ፎቶ አንስተህ ትልክልኛለህ። የታተመበት አመት ከተገለፀ እሱንም ፎቶ ታነሳልኛለህ። በፕሮፌሰር ግርማ ሙልኢሣ ዙሪያ መጻፍ ያለብህ የተለየ መረጃ ካለም በሳቸው ስር ያለው ገፃቸው ክፍት ነው።
አንተ ያሉህ ሁለት መጽሐፎች እኔ ያስገበኋቸው ከሆኑ፣ እስካሁን ያልኩህ ሁሉ ለሌላም ሰው ስለሚሰራ እና አንተ ቤተሰብ ሆነህ ስለምትቀጥል በዛ መንፈስ የተብራራ ነው።
ሰው ቤተሰብ ሳረግ የምሬን ነው። መልካም ቀን!!!! ከላይ ከ10 ዓመት በኋላም አረሳህም ብዬህ አይደል። ያነቃቃኝን ብዙ ያስለፈለፈኝን ነገር ልንገርህ Artemis II ወደ ጨረቃ ጉዞ ላውንች የሚደረግበት ቀን ላይ 1 ሰዓት ከ14 ደቂቃ ሲቀረው ነው ያንተን ኮመንት ያነበብኩት። በህይወት ዘመናችን አንድ ሁለቴ ሊገጥም የሚችል ነገርን በእማኝነት በምናይበት ቀን በቀኑ ያደረኩትን ነገር ሁሉ አንዱንም የምረሳው አይመስለኝም። ከተሳካ ልጆቻችን ትምህርት ቤት የሚማሩት ጉዳይ ነው። ቢያንስ ሁኔታውን በቲቪ ላይቭ ተከታትዬ ነበር ልንላቸው ይገባል ሃሃሃሃ ጨረቃን ባይረግጡም ጨረቃን ሲዞር አብሪያቸው ዞሪያለሁ ማለት የአባት ነው ሃሃሃሃ የግርጌ ማስታወሻ ገና አላገባሁም ልጅም የለኝም ሆኖም ዛሬ ሙሉቀን እንዲህ ሳስብ ነው የዋልኩት ሃሃሃሃ በዚህ መመሰጥ ውስጥ ሆኜ ነው ዛሬ ያገኘኸኝ ደና እደር!!! ብዙ ስለፃፍኩ የማቅህ መስሎኝ ነገ ደውል ልልህ ነበር ሃሃሃሃ
ረስቼው ነበር። የፕሮፌሰር ግርማን ፎቶ የተጠቀምኩት በተማሪነቱ እስራኤል ዶርም ውስጥ የተነሳውን ነው። አማራጭ ፎቶ የምታገኝም ከሆነ እባክህን ብያለሁ።
እርዮትዬ አይንሽ ነው በለኝ ወላሂ አላመንኩም። አምስት ወር ብለኸኝ ስለነበር አዲስ ነገር አይኖርም ብየ ምን እንዳመጣኝ እንጃ ወላሂ በጣም በጣም በጣም ነው ደስ ያለኝ ደሞ ሁሉ ነገሩ ሲያምር እንዲህ አልጠበኩም ነበር። የቃሉ ሰው እውነትም ወላሂ እጅግ ነው ደስ ያለኝ።
ReplyDeleteሰዪ ያው እንደዛው ነው።
Deleteሪታ ጉስታቮ ይልሃል
ReplyDeleteጃ ይሄንንስ እንዴት ታየዋለህ? አንድ እንዳንተ ጥበብ የጠራችው ጎረቤቴን ዌብሳይትህን አሳየውት። "እንዴ ይሄ ሁሉ ደራሲ እዚ አገር አለ እንዴ?" እያለ ጭንቅላቱን ወደ ጎን ሲነቀንቅ ሲነቀንቅ ሲነቀንቅ..... "ይሄን ሁሉ ደራሲስ እኔ እንዴት አላውቀውም?" እያለ ከንፈሩን ሲነክስ ጥርሱን ሲያፏጭ በመሃል ዝምብሎም ፉጨት ሲያፏጭ ሲያፏጭ ሲያፏጭ.... አሁን ጭንቅላቱን የነቀነቀበት አንገቱ በጀሶ ታስሮ ቁጭ ብሏል ሃሃሃሃሃሃሃሃሃ ካሳ ያስፈልገው ይሆን? ጥበብ የጠራችው ሰው እንዲህ አንገቱ ከተቀጨ እኔ ግንበኛው .... አገኘኸኝ? ሃሃሃሃሃ አሁንም እደግመዋለሁ እንደ ልጅ ወስደህ አሳድገኝ። ሳድግ አንተን መስዬ ነው ማደግ የምፈልገው። ጃ ሙት እንደዚህ አትወድም አደል? ጥግ ድረስ ትችላለህ!!!!!!! ለቅዳሜያችን ስትል መልስ አልፈልግም።
ReplyDeleteሃይ ፍሊጶ መቼስ ቅዳሜ አንብቤ ለገለፈጥኩበት ኮመንት ዛሬ ሐሙስ ላይ "ሃሃሃሃ" ብዬ አልጀምርም። ታክሲ ውስጥ በጣም ኮስቴ ብለው ሃሃሃሃ የሚል ኮመንት የሚሰጡ ሰዎች ስለሚገርሙኝ ነው። እነሱን አልሆንም መቼስ። ምን አሳየህ የነሱን ኮመንት እንደምትለኝ አልጠራጠርም። ምን ልይ ታድያ ወንድሜ? ታክሲ ውስጥ ቲቪ አይከፈት? ወደ ጉዳዬ ስሄድ....
Deleteለቅዳሜ ስትል እለፈኝ ስትል አልፌህ እንደነበር እሙን ነው። ምን ያህል የሰው ስሜት እንደምጠብቅ ተረዳኸኝ ኣ? ሆኖም ከታች ያለው አስተያየት ሰጪ አስተያየት ሰቶኝ አስተያየት ሰጥቼው ነበር። መደሚደሚያው ምን ሆነ መሰለህ? "ከላይ ያለው አስተያየት ሰጪ አሳስቶኝ ነው። እሱ እንደ ልጅ አሳድገኝ ሲል ስሜት ውስጥ ገበቼ ተነሳስቼ የፃፍኩት ነው" አለኝ። በመለጠቅም አስተያየቶቹ ይመቸኛል ብሎ አድንቆሃል። ብቸኛ የሚሳፈጥህ ሰውም ብሎ አክሎበታል። ይሄን ሌላ ጊዜ እንደርስበታለን።
አሳሳተኝ ሲለኝ እባብ መሆንህን ባቅም፣ ብዙ ሄዋናትን እንዳሳሳትክ ባቅም አዳሙ ላይ መድረስህን ግን ዛሬ ሳውቅ አንተ እባብ ሃሃሃሃሃሃሃ
በዛው ይሄን ጥያቄ ጠይቄህ ነው የማበቃው። መልሱ ወይ አንተ ዘንድ አልያም ጋሽ ዳኒ ጋር ነው ያለው። ለኔ ከአዕምሮዬ በላይ ነው። ምን መሰለህ እናንተ የምትቀመጡባት ካፌ (ካፌ ካፌ ካፌ ያው ካፌ) አጠገብ ያለው ፔንስዮን ማስታወቂያ ለጥፏል። ማስታወቂያው ባጭሩ [ለክቡራን ደንደበኞቹ - የአድራሻ ለውጥ ማድረጉን እና የአዲሱን ቦታ አድራሻ የሚጠቁም ነው] .... እንግዲህ ይሄ ነው ያልገባኝ። የፔንሲዮኑ ደንበኞች ምኑን ተከትለው ነው ወደ አዲሱ አድራሻ የሚሄዱት። ምግብ ቤት ቢሆን ሙያቸውን ተከትለው ልንል እንላለን። በጣም ግራ ስለገባኝ ነው። አውቃለሁ መልሱን እናንተ ታውቁታላችሁ ፋራ የቤት ልጅ ብላቹም መርቁኝ ሃሃሃሃሃ ግን መልሱን ንገሩኝ። ያላወኩት ነገር ይከነክነኛል ሃሃሃሃ
በነገራችን ላይ ኤርሜ ይሄን ማንቆለጳጰስህን ትትህ የምትሰጠው አስተያየት እኔም በእጅጉ ይመቸኛል። ደጋግሜ የምታወራበትን መንገድ ወደ ጽሑፍ አምጣው የምልህ የምሬን ነው። በጣም ስለሚለይ ነው። ሄዋናት የሚሰምጡልህ በደሞዝህ ይመስልሃል? ሃሃሃሃ ከታች ያለው ወዳጄ ይሄን ገንቢ አስተያየት እንድሰጥህ ስላደረገኝ ገንቢ ገንቢ ምግብ ይስጠው ብያለሁ። አበበች ጎበና ስላደረከኝ ግን አላመሰግንም ሂሳብ እናወራርዳለን ሃሃሃሃሃሃሃ ይመቻቹ ብቻ!!!
እርዬ እንኳን እንኳን እንኳን ደስ አለህ ጓደኛዬ!!! አይ ዊሽ እዛ ኖሬ ቢሆን ኖሮ
ReplyDeleteማሂዬ እንኳን አብሮ አብሮ ደስ አለን!!!!!! ደስታሽ የእውነት ነዝሮ ተሰምቶኛል!!!!! በዚ ጉዳይ ካንቺና ከሰዪ የማስቀድመው ሰው አልነበረኝም። ሰዪ እንኳ ከኮመንቷ በኋላ ነው ቀድሜ መሄዴን ያወቀችው። ማሂ ሙች አጉድላችሁኛል። ለአንቺም ለተስፍሽም አንድ መልህክት ሰዪ ታደርስሻለች። እስከዛው ተስፍሽን ጉንጩን በይልኝ በቦክስ ሃሃሃሃ ለካ ሰፈሩን የምወደው እናንተን ይዞልኝ ስለነበር ነው .... ተይው ብቻ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
Deleteእሪ ስንት ጊዜ ሼር ሳደርግ ነው የምታመሰግነኝ። ሶሻል ሚዲያ ላይ ልመልስህ ሁሉ ታጥቄ ነበር። ለውለታዬ ምላሽ ሙሉ ፖስት እጠብቃለሁ።
ReplyDeleteአንትሽ አንትሽ አንትሽ አንት የቁምነገር ቋት እንዴት ነው በአያሌው? አንተ ነህ ለካ ትራፊኩን ያጨናነከው ከድሮም እኮ አንተ ትራፊክ ላይ.... ሃሃሃሃ አንትሽ ይገርምሃል ዌብሳይቴ ፌስቡክ ላይም ሌላ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሼር ሲደረግ አውቃለሁ። ግን እኔ ሶሻል ሚዲያ ስለሌለኝ ማን ሼር እንዳረገው ምን እንደተባባላቹ ምንም ነው የማላውቀው። ምንም። እኔ ለነፍሱ ያደረ አንድ ግለሰብ ብዬ ዋጋህን ለሰማይ ቤት ሳረግልህ ነበር። አንተ መሆንህን ካወኩ ዘንዳ ግን ምድራዊ ዋጋህን በምስጋና ብቻ አይበቃም ሰራተኛ ደሞዙ ይገባዋል እንዲል ታላቁ መጽሐፍ ዝምብለህ ሼር አርግ ብቻ! ፍፃሜህ ታላቅ ይሆናል ሃሃሃሃሃ ስለመዘግየቴ አፉ በለኝ አሁን ከመሸም ነው ያየሁት ነገ ደዋይ ነኝ።
Deleteመጀመሪያ ያሰብኩትን ልንገርህ "ይሄ እኮ በተቋም ደረጃ ሊሰራ የሚገባው ስራ ነበር!"... ትንሽ ቆይቼ አንተ ራስህ ብቻህን ተቋም መሆንህ ሲገባኝ፣ በልቤ "የተቋምን ስራ ራሱ ተቋም ሰራው" አልኩኝ። ስለጠፋህ ድንገት መጥቼ ነው ያየሁት። የዘገየሁት ደግሞ ሳጣራ ነው። እንደ አቅም ያሉኝ መጽሓፍትን አንድ ባንድ ፈትሻለሁ። ማስታወሻዬንም ቼክ አድርጊያለሁ። እና እጅ ልነሳ ብቻ ነው የመጣሁት። ሲገባኝ በሱስ ህይወትህ፣ በንባብ ህይወትህ ያደረከውን አይቼ "ይሄ ልጅ መንገዱ ሁሉ ለፍሬ ይሁን!!" ተብሎ ተመርቋል እላለሁ። በምርቃት አምናለሁ? እኔንጃ! አንተ ግን መንገድህን ሁሉ ውብ ማድረግ ትችልበታለህ። ይሄ መታደል ነው። በጣም አንባቢ ነኝ ለሌላው አንባቢ ተጨንቄ አውቃለሁ? አላውቅም። አንተ ግን ለሌሎች መንገድ ስለመጥረግ ትጨነቃለህ። አቦ ነፍስህ እንዴት ትረካ? የውነቴን ነው እጅ ልነሳ ነው ዛሬ የመጣሁት። "በወጉ አያከብርም በወጉ የማይንቅ" እንዲል በዕውቀቱ ስዩም እንኳን እጅ ለመንሳት ለማድነቅ ሩቅ ነኝ። እናቴ ትሙት! ሰው ግን አውቃለሁ። እለያለሁም። "that's what I do, I drink and I know things." እንዲል Tyrion Lannister..... ዛሬ እጅ ልነሳ ነው የመጣሁት። ስለ ነገ ነገ ራሱ ቢያቅም ድካምህን የሚያቀል ነገር እንደምዘረጋ ግን ቃል ገብቻለሁ። ይቺ ፅዋ ምስክሬ ናት።
ReplyDeleteእያዩ በሆነ በማላውቀው ሰው ድምጽ ነው ያነበብኩት። ከዛ ያወኩት መሰለኝ ግን አላውቀውም። ብቻ በድምጽ ነው ያነበብኩት። ምን እንደምልህ አላውቅም ደጋግሜ ሰው ሳመሰግን ይሰለቸኛል። ይህ የምስጋና ጥጌ ነው። የሆነ ኮመንት ካንተ በልቤ ስጠብቅ ነበር ... ካረሳኸው ታርጌት ያልኩህ። እነሆም ሆነልኝ። ነገሮችን የምትለካበት መሳሪያ ሲኖርህ ጥሩ ነው። እያልኩህ ያለኸው ይገባሃል። እጅ መንሳት ምናምኑን ተወው እንደውም የሚጎረብጠኝ ጉዳይ ነው። ግን አጠቃላይ ስሜቱን እረዳለሁ። ኮመንትህ ምን ማለት እንደሆነ በጨመርክልኝ ኢነርጂ ልክ ታየው ነበር። ባካል ባታየኝም የሆነ የጨመርከው ነገርን ግን ሁሌም አትርሳው። ሌላ ምን ልበልህ? ከዚ በፊት ባመሰገንኩህ ልክ ማመስገን ይሰለቸኛል። በቃ እንደውም በቃኝ። ይህ የምስጋና ጥጌ ነው።
Deleteበ1955 ያለ ጭንቀት እና ብስጭት የመኖር ዘዴ የሚል መጽሐፍ መኖሩ በጣም ነው የገረመኝ። አትጨነቁ አትጠበቡ የሚሉ መፅሐፎች በዚ ዘመን ብቻ የፈሉ ይመስለኝ ነበር። ትርጉም ነው?
ReplyDeleteሰላም ቤዚ እንኳን በደህና መጣሽ!!! መጽሐፉ ትርጉም አይደለም። አንቺ ባልሺው መንገድ ልብ አላልኩትም ነበር። ጥሩ እይታ ነው ያለሽ። የመጀመሪያ መነፅርሽ ስለተመቸኝ ቀጣይም ቤቴ ቤትሽ ይሁን ብያለሁ። ተፈራረምን ሃሃሃ እኔ የገረመኝን ልንገርሽ የመጽሐፉ ጸሐፊ ሥዩም ተክለሃይማኖት የሐረር ሰው ነው። 'ሐረርና ድሬ ከድሮም ነው እንዴ ጭንቅ የማይወዱት ?' ብዬ ነበር በሆዴ። ቀይ ይሄ ነገር በዘረመል የሚተላለፍ ከሆነ አብረን እናጠናዋለን ሃሃሃ በድጋሚ ስለመጣሽ ደስ ብሎኛል!!!
Deleteዌብሳይትህን እየጎበኘው ማንን ባይ ጥሩ ነው? ቢኒ ቹፔን እንዴ ብዬ ተጠግቼ ሳይ ስሙ ሌሊሳ ግርማ ይላል። ሪታ ሙት በጣም ነው የሚመሳሰሉት። ዘመድ ይሆኑ? ቢኒ ቹፔ የት ነው ያለችው ግን ትገናኛላቹ? ከተገናኛቹ በጣም ሰላም በልልኝ።
ReplyDeleteሃሃሃሃሃሃሃ እጢህ ዱብ ይበል እጢዬን ዱብ እንዳረከው ሃሃሃሃ በስማብ እንዴት እንደደነገጥኩ... እጅግ የብዙ ሰዎች ፎቶ በፎልደር በፎልደር ስላለኝ የቢኒን ፎቶ ተሳስቼ ያስገባው ነው የመሰለኝ። እንዴት ሮጬ እንደሄድኩ። ጭራሽ በድንጋጤ መጀመሪያ ሳየው ፎቶው እኔንም የቢኒ ቢመስለኝስ?... የስራህን ይስጥህ ብቻ ሃሃሃሃሃሃ ተመሳሳይ ሸሚዝ ነበራት መሰለኝ በችኮላ ተመሳሰለችብኝ ሃሃሃሃሃሃሃ ተረጋግቼ ሳየውም የሆነ የሚመሳሰሉበት ነገር አላቸው። ጥሩ አመሳሳይ ነህ ማለት ነው። ቢኒ ይሄን ካየሽ ጥበብ በመንፈስ እየጠራችስ ነውና ወዬ በያት ይሄ ዋናው ምልክቱ ነው ሃሃሃሃሃ
Deleteአሁን ተረጋግቻለሁ አንተ ግን ማነህ???? ሃሃሃሃ ጭራሽ ሰው እንደፈለገ ነፃ ሆኖ አስተያየት ይስጠኝ ብዬ አኖኒመስሊ እንድትኮምቱ ብፈቅድ በመላምት ጨረሳችሁኝ እኮ! እንትና ይሆን? እንትና ትሆን? እያልኩ። እከሌ ነኝ ያባት ነው እረ እባካቹ ሃሃሃሃሃ ሎማንኛውም ቢኒ ደና ነች። አባት ሀገር ጀርመን ነዋሪነቷን ካደረገች ቆየች። ከሶስት ሳምንታት በፊት በስልክ ተገናኝተን ነበር። ቀጥሎ ስንገናኝ አኖኒመስ በጣም ሰላም ብሎሻል እልልሃለሁ ሃሃሃሃሃሃሃ ማንም ሁን ብቻ እጢ ዱብ ይበል አቦ ሃሃሃሃሃ ይልመድብህ።