Komentar baru

Advertisement

ትመጫለሽ ብዬ........

Eriyot Alemu
Oct 9, 2024
Last Updated 2024-10-09T18:26:46Z
Advertisement

 


ዝምብዬ ሳስበው ሳስበው ግን "ትመጫለሽ ብዬ..." የሚለው የሕዝብ መንቶ ግጥም ሲጀምር ብዙ ሰው ቀድሞ የሚያስበው "ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ"ን ብቻ ይመስለኛል፡፡


ገብረክርስቶስ ደስታም “ቀረሽ እንደዋዛ" ግጥሙ ላይ ተጠቅሞታል፡፡

"ትመጫለሽ ብዬ ሳይ ማዶ ሳይ ማዶ 

የልጅነት ዓይኔ ሟሟ እንደ በረዶ"


ግን ሌላም አንጀትን የሚያላውሱ ትመጫለሽ ብዬዎች አሉንኮ።


ትመጫለሽ ብዬ በሬን ባልዘጋው 

ከፍቶት አድሯል ብሎ ማን ጠየቀኝ ሰው 

(ሕብረ ቃሉን አውጡ ሃሃሃ)


ትመጫለሽ ብዬ ከማዶው በላይ 

አንገቴ ረዘመ ቆሜ አንቺን ሳይ ሳይ


ትመጫለሽ ብዬ አሻግሬ ሳይ 

አንቺ ልጅ ማለፊያ መንገድ አጣሽ ወይ


ትመጫለሽ ብዬ መንገዱን አላምነው 

የሚመላለሰው ሌላው ሌላው ሰው ነው


ትመጫለሽ ብዬ ነጠላ ስቋጭ 

ምን ትጠቀሚያለሽ አንገቴ ቢቀጭ



የመጨረሻውን የገጠመው ሰውዬ ሴቶች አንዴ እንኳ በስህተት "ትመጣለህ ብዬ…" ሲሉ ባለመስማቱ… ራሱ በቁጭት ነጠላውን እየቋጨ ገብቶበት ይመስለኛል ሃሃሃሃ በናትሽ ምጪለት አንገቱ ከሚቀጭ ሃሃሃሃ (የመቋጨት ልምድ ያላችሁ ግን ይህ ከላይ ያለው ቋጪ በትክክል ምን ማለት እንደፈለገ ብትነግሩኝ አይከፋኝም፡፡ ባትነግሩኝም አይከፋኝም)


በዚህ አጋጣሚ ግን አያቹ ሴቶች ምን ያህል ጠባቂ እንዳልሆኑ ... ቀጥታ እንደ መሰሉ ፋንታሁን "ወይ ልምጣ ወይ ምጣ" ብለው ነው የሚዘፍኑት።


ተያይዞም አንድ ግርም የሚለኝ የቅብብሎሽ ዘፈን አለ፡፡ እትዬ ሒሩት እና ጋሽ መሃሙድ ናቸው የሚዘፍኑት። ለመሃሙድ ጋሽ ማለቴ ካልቀረ ነው ለሒሩትዬ እትዬ የጨመርኩት እንጂ… እቤት እቤት ልክ እንደ ቡዙዬ እሷንም ሒሩትዬ ነው የምላት ሃሃሃ


እሷ… 

"ተው ዘገየህ አንተ ሰው ዘገየህ ተው ዘገየህ አንተ ሰው ዘገየህ 

እመጣለሁ ብለህ ልቤን እያጋየህ ተው ዘገየህ አንተ ሰው ዘገየህ" ትለዋለች።


እመጣለሁ ስላላት ነው የምጠብቀው እንጂ ከላይ እንዳሉት እንደ ሞላ ወንዶች፣ ዝምብላ በመላምት 'ትመጣለህ ብዬ' እያለች አትጠብቀውም። ወንዶች ከዚ ብዙ ሊቀስሙ ይገባል ባይ ነኝ፡፡ እንደውም ወንዶች ግልፁን ሊነገራቸው ይገባል። በመላምት ሰው አጠብቁ። ተመከሩ ብያለሁ… በኋላ እንደኔ ጣፋጭ ጣፋጭ የምክር ዘለላውን የሚያካፍላቹ አታገኙም ሃሃሃሃ


በመላምት ሰው የምጠብቁ መጨረሻችሁ የደበበ ሰይፉ “ጠብቄሽ ነበረ" ግጥም ነው የሚሆነው


ጠብቄሽ ነበረ 

መንፈሴን አንጽቼ 

ገላዬን አጥርቼ 

አበባ አሳብቤ 

አዱኛ ሰብስቤ 

ጠብቄሽ ነበረ፤ 

ብትቀሪ ጊዜ፣ 

መንፈሴን አሳደፍኩ 

ገላዬን አጎደፍኩ 

አበባው ደረቀ 

አዱኛው አለቀ፤ 

ብትቀሪ ጊዜ፣ 

የጣልኩብሽ ተስፋ 

እኔን ይዞኝ ጠፋ።


ተመከሩ ብያለሁ ተመከሩ ሃሃሃ


ታድያ ጋሽ መሃሙድም… ኮራ ጀነን ብሎ… 

"ና ካልሺኝ አልቀርም የኔ አለም ና ካልሺኝ አልቀርም የኔ አለም 

ስላንቺስ የማልሆነው የለም" ይላታል፡፡ እንዲህ ነው ወንድ ልጅ መሆን ያለበት፡፡ አሞቱ ኮስተር ያለ ወንድ እወዳለሁ ሃሃሃሃ ዝም ብለው ና ሳይባሉ የሚሄዱ ነፈዞች ያበሽቁኛል ሃሃሃሃሃ ሆኖም መጀመሪያ "እመጣለሁ" ብሎ ያላት እሱ ሆኖ "ና ካልሺኝ አልቀርም" እርስ በእርሱ ቢወሳሰብም፣ ዋናው ፍቅሩና የሁለቱ መግባባት ነው ብለን እናልፈዋለን፡፡ በፍቅራቹ መሃል ነፋስ አይግባ ብሎ መመረቅ እንጂ እንዲህ ስር መግባትም አያስፈልግም ሃሃሃሃ



ግን ግን ጨዋታው ጨዋታ ነውና "ትመጫለሽ ብዬ" ትንሽ ዘወር ተደርጎ በሚካኤል በላይነህ "ትመጪ እንደው እያልኩ" ተብሎ የተዘፈነው ዘፈን… በትመጫለሽ ዘርፍ የሚስተካከለው ያለ አይመስለኝም፡፡ "ትዝታም አይደለም ተስፋ ነው ቅኝቱ" የሚለው አንጓ ምን አይነት መንፈስ የሆነ አገላለፅ ነው ያስብለኛል ሁሌም ሳስበው ሳስበው፡፡ ይሄ ዘፈን ቀን ቀን እየገፋ፣ ዕድሜዬ እየታለበ ስንቴ እንደሰማሁት ስንቴ እንደገረመኝ… እኔና ጆሮዬ ነን የምናውቀው። ዝም ብዬ ባልፈው ጆሮዬ ይታዘበኛል ብዬ ነው እንጂ ዛሬ በማካበድ ሙድ ላይ አልነበርኩም ሃሃሃሃ


ሌላው በማሳዘን፣ አንጀት በመብላት፣ በቅላፄ የሚከተለው የባህታ ገብረህይወት “አሁንም እዛው ነኝ" የሚል ዘፈን ነው….


“ምናልባት ብትመጪ እንዳይጠፋሽ ቤቴ 

አሁንም እዛው ነኝ የፍቅር እመቤቴ 

ጊዜን መስሏል ብለሽ ሃሳብሽ እንዳይጠም 

እንኳንስ ፀባዬ ልቤም አልተለወጠም 

እስቲ መጥተሽ ራርተሽ ናላሽ ይታዘበኝ 

በእድሜ ካልሆነ በሌላው እዛው ነኝ፡፡"


አስቡት መጥታ እንዳታጣው ከሰውነት ወደ ዛፍነት ሲቀየር… በዜማ የማታውቁት ይኧው ስሙትና ልባችሁ ቅልጥ፣ እዝን፣ ኩርምት ይበል ለሱ....



የወንዶችን ጠባቂነትን በግጥም እናሳርገው ...


ኑረዲን ኢሳ… “ሰው እንዴት በሁለት መስመር እንደዚህ ልቦለድ ይፅፋል?” የሚያስብለኝ ግጥም አለው፡፡ ባሰብኩት ቁጥር ግርም ድንቅ ጥልቅ የሚለኝ ግጥም ነው፡፡


“ምን ያህል ሆኖ ነው ምን ያህል ስንት ዕድሜ 

ሳር የበቀለብኝ ስጠብቅሽ ቆሜ"


ሴቶች “ትመጣለህ ብዬ.." አይሉም ብዬ እንዳልምል ይቺ አስቱካ “የኔ ቆንጆ” ዘፈኗ ላይ ቀጣዩን ትሰነቅራለች…


ትመጣለህ ብዬ ድንጋዩን ስለቅም 

እንደወጣህ ቀረህ ያንተን ሆድ አላውቅም


እዚሁ ዘፈኗ ላይ ታድያ ቀደም ብላ… “አትምጣ ግርሻ ትሆንብኛለህ.." ስለምትለው... ልጁን ይመጣል ብላ ድንጋይ የምትለቅመው ልትፈነክተው ነው ወይ? አያስብልም ትላላችሁን? ሃሃሃሃ


በመቀጠል ደሞ "አልመጣም!" ስለሚሉቱ ስለምንማማር እስከዛው.. "አልመጣም ቀረሁኝ —ሸጌ— አልመጣም ቀረሁኝ ካንቺ የተሻለ— ሸጌ— እዚህ አገኘሁኝ" የሚለውን ብትፈልጉ በተሾመ ምትኩ ብትፈልጉ በኃይለየሱስ ግርማ ብትፈልጉ በስለሺ ደምሴ የተሰሩትን እንደምርጫቹ እያዳመጣቹ ቆዩኝ...


iklan
Comments
  • Stars Rally to Beat Predators in Winter Classic at Cotton Bowl

8 comments:

  1. ተዋ እሪ! በመላምት አትጠብቁ ብለህ ትመክራለህ አይደል? እኔ አለው አይደል ያለሁበት ሀገር እንደማትመጣ እያወኩ አንተ ያለህበት እንደማልመጣ እያወኩ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆኜ …. ትመጣለህ ብዬ ….. ውጪ ውጪውን የማይ ምስኪን! ደሞ ሰሞኑን የሆነ አስተያየት ተሰቶክ ያጠፋዋል አያጠፋውም ስል አጥፍተከዋል… አቦ ተይአ በለኝ ናፍቆኛል። ሁሌም መልካሙን!

    ReplyDelete
    Replies
    1. ፈንዱሼ ሌላ ጊዜ አቦ ተያ የምለው ጭንቀቴን ነው ዛሬ ግን ምን ያህል እንደምትረጂኝ ስለማውቅ አቦ ተይአ የምልሽ በረፍት ስሜት ነው። ሜሪዬ በዚ ጉዳይ ሌላ ምንም አልበልሽ!!!!!!!!!!!!!

      አስተያየቱን ካየሺውማ ላብራራው ሃሃሃሃ የአስተያየቱ አጠሪራ "ከአንዲት ፍሬ ልጅ ጋር ሲኒማ ቤት አየሁህ ተው አግባ" ነው የሚለው። ኡዝባኪስታንኛው ከአንዳንድ ፍሬ ልጆች ጋር ከምትንዘላዘል ለምን አታገባም ነው። እኔም እስማማለሁ።

      ሲጀምር ግን ልጅቷ ሶስተኛ ድግሪዋን በመስራት ላይ ያለች እጩ ዶክተር ነች። እንደኔ እድሜዋን አተመስልም። ሲቀጥል ግንኙነታችን ትምህርታዊ ነው። ወንድምና እህት ይሰለቻል ብዬ ነው ሃሃሃ ሲሰልስ ሰው እንደፈለገ ያስበኝ እንጂ ህይወቴን አላብራራም ስለምል፣ እንደ አስተያየት ሰጪዋ አተራማሽ አርገው የሚያስቡኝ አሉ። እኔን ጭምቱን ሃሃሃሃ በጣም ጭምትም የሚያረጉኝ ደሞም አሉ። ከቶ እኔ ማነኝ ሃሃሃሃ

      ሜሪዬ እኔ ለትዳር ያለኝን እጅግ ቀና አመለካከት አታውቂምን? መንዘላዘልንም በዛው ልክ እጠየፋለሁ። ወንደላጤ መሆን ማለት ትዳርን መጥላት፣ መንዘላዘል መምረጥ ለሚመስለው ሁሉ አስረድቼ አልችለውም ብዬ ነው። ገና በካላንደር አቆጣጠር 40 ሳንገባ ንዝንዙ በዛብኝ። በዛ ላይ ከእግዜር ጋር ተከራክሬ ያስመለስኩት 10 አመት አለኝ። አስቢው እንዴት አንድ ፍሬ ልጅ መሆኔን ሃሃሃሃሃ ሜሪ አንቺ ሆነሺብኝ ነው እንዲህ ያብራራሁት ማርያምን!!!!!!!!!

      Delete
  2. ገርጂ ካንተ ጋር የማያት ድሬዷ ልጅ ሰአሊ ነች?

    ReplyDelete
    Replies
    1. በለው ከማለት ውጪ ምን ይባላል? ቦታ አመራረጦትን ደሞ አድንቂያለሁ ሃሃሃሃ ወደ ጥያቄዎ ስገባ ቀድሜ ይሄን ልሎት ወደድሁ…

      አንድ ሰው መንገድ ላይ አግኝትዎት “ሰዓት ስንት ነው?” ቢልዎ “ለምን ፈለከው?” ይሉታልን? ይሄን እንዲሉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነትዎ አይፈቅድሎትም አይደል? ስለዚህ በትህትና “የራስህን ሰዓት ግዛ እንጂ” ይሉታል ሃሃሃሃሃ

      እናም ጠያቂዬ ገርጂ ላይ ከኔ ጋር የሚያይዋት ድሬዷ ልጅ ሰዓሊ አይደለችም። አመሰግኖታለሁ!

      Delete
  3. እርዬን የበላው ጅብ እንብላ አያውቅም እንዴ? ደስታህ ደስታዬ እንደሆነ ታውቃለህ እንኳን ደስ አለህ እንዳልልህ እንኳ ሊቨርፑል ዋንጫ ከበላ በኋላ ጭልጥ ብለህ ነው የጠፋሃው። ተስፍሽ ዋንጫው የታወቀ እለት ከነገ ጀምሮ እዚች ድርሽ አይልም ሲል ልብ አላልኩም ነበር። ሲቆይና እውነት ሲሆን ነው ሚስጥሩን የነገረኝ። ሊደብቀኝ ይገባል ሚስቱ አይደለው? እርዬ እንኳን ይሄን አግኝቼ አይደለም በሱ ጉዳይ ከሚነዘንዙህ መሃል አይደለው? አበራ ይሙት እስኪሆን ድረስ አልተውህም። ስለዚህ አረሳስቶ መምጣት የሚባል የለም። ስለማይቀርልህ ቶሎ ና።

    ReplyDelete
    Replies
    1. ማሂዬ ማሂዬ ማሂዬ አንቺ ልከሽብኝ እቀራለሁ ወይ? ወይ ወይ ወይ ሶስቴ ሃሃሃሃ ደሞ ቶሎ ና የሚል ዘፈን አለ መሰለኝ ጆሮዬ ላይ አቃጨለ ሃሃሃ ቢዚ ሆኜ ጅቡ በልቶኝ ሊቨርፑል ዋንጫ በላ እንዴ? ሃሃሃሃ በዚ አመት አንድ ጨዋታ ብቻ እኮ ነው ያመለጠኝ…. እንኳን እንኳን አብሮ ደስ ያለን ቤተሰብ!!!!!!

      ማሂነት መንቀልቀሌን ላስረዳ… ከ8ኛ ክፍል ጀምሬ እስከአሁን ለ20 ምናምን አመታት ሊቨርፑልን በታማኝነት ደግፌያለሁ። ለራሴ እስኪገርመኝ ድረስ ድሮ ቃማቴ ሆኜ እንኳ ከጫት ላይ ተነስቼ የሊቨርፑልን ኳስ ያየሁበት ጊዜ የትየሌለ ነው። ከጫት ላይ ተነስቼ የሰራሁት ሌላ ቁምነገር ምንም ትዝ አይለኝም። የሚያውቁኝ ሁሉ ይሄን ያውቃሉ። በነዚህ ሁሉ አመታት ውስጥ ታድያ ሊቨርፑል ፕሪምየርሊጉን ያነሳው ሁለቴ ብቻ ነው። ዘንድሮ እና ከአምስት አመት በፊት። እና ሊቨርፑል ዋንጫ በበላ ባመቱ… የሚል ሞቅታ ውስጥ ብገባ ይፈረድብኛል ወይ? ወይ ወይ ወይ ሶስቴ ሃሃሃሃ

      ማሂነት አስተያየት ቦታ አመራረጥ እያስደመማቹኝ ነው ደሞ ሃሃሃ አስቢው እስቲ ቃሌን ጠብቄ አዳራሹ ላይ “ዚስ ኢዝ አንፊልድ” ብዬ ሳፅፍ… እነ ተስፍሽ ከበው “ዩ ዊል ኔቨር ዎክ አሎን” እያሉ ሲዘምሩ ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ አሰብኩት በስማብ ሃሃሃሃሃሃሃሃ ማሂነት ለንዝነዛው ሁሉ ተዘጋጅቼልሻለሁ። እህቴ ማለት እኮ ነሽ። በኔና በቤቴ እጅግ ትልቅ ቦታ አላቹ ከነባለቤትሽ። የሰርግ ጥሪ አስመሰልኩት ኣ ሃሃሃሃ እንዳትሰለቺ ወጥሪኝ ሃሃሃሃ ላለመዋሸት ተስፍሽ እውነት አለው አንዳንዴ ቆቅ የሚሆነው ነገር አለ። ጅግራ የማይሆነው ግን እንዳንበላው ነው እንዴ? ሃሃሃሃሃሃሃ መቼስ ታውቃላቹ ያን ጃኬት የሚያስለብስ ሙድ ውስጥ ገብቼ ነው። ሰሞኑን ግን መጪ ነኝ። የማልቀረውን ስልሽ ሃሃሃሃሃሃ

      Delete
  4. ሃይ ሳምሪ በቃ ፌስቡኮች ምንም መዝናኛ የሌለን ነው ኣ የሚመስላቹ? ምን ላይ ናችሁ ግን? ዮኒ እንዳጨወተኝ ከሆነ ወቅታዊ ትኩ ሱ አጀንዳ ''ዲያቆን ከድር ሕዝቡን የዝንጀሮ ቂ* ሁላ ብሎ ሰደበው'' ነው። ባለጌ ነው ቢያንስ እንዴት መቀመጫ አይልም ሃሃሃሃሃሃ አንዳንዴ አንጀቴን ትበሉታላችሁ እኮ... ለዚ ጎራ ለይታችሁ ሙያዊ ትችት ስትሰጣጡ ከሩቅ ሆኖ ለሚያያቹ በጣም ነው አንጀት የምትበሉት። ይሄን ነው እነ ዮኒ ተዝናና እንጂ የሚሉኝ። ለማንኛውም ይመቻቹ... እንደገና ሎማንኛውም ዛሬ የማየው ዩኤስ ኦፕን የቴኒስ ፍፃሜ አለ። ኮኮ ጋኡፍ እና ሳባሌንካ ተጋጣሚዎቹ ናቸው። የጋኡፍ ደጋፊ ነኝ። ድሮ በኛ ዘመን ቲቪ ጣቢያዎች እንዲህ ሳይበዙ በፊት ቲቪ አፍሪካ የሚባል ጣቢያ ነበር። ያኔ ነው ቴኒስ የተከተብኩት። ነጥብ እንዴት እንደሚሰጥ ህግጋቱን ያኔ ነው ራሴን በራሴ ያስተማርኩት። እና ጋኡፍ ቬኑስ ዊሊያምስ እና ሴረና ዊሊያምስ የተባሉ እህትማቾችን ስለምታስታውሰኝ ይመሰለኛል ደስስ ትለኛለች። ሳምሪ አየሽ የኔን መዝናኛ? የግሌ ነው ከትዝታዬና ከራሴ መንገድ የሚቀዳ ነው። የኔን መዝናኛ ለሰው የማሳየውም የማወራውም አይደለም። ለራሴ የምኖረው ነው። ትዝታዬ የማረገው የግሌ ነው። ሃገሪቱ ያለችበት ሁኔታ እንዴት እንደሚያሳስበኝ ታውቂ አይደል? በዚ በዚ ባላንስ ካላረኩ ራሴን እጎዳዋለሁ። ክፍል ሁለት ሃሃሃሃሃ ሳምሪዬ ዲያቆን ከድር አርቲስት የኔነሽ እያልኩ ለመቆየት ግን ሞራሉ የለኝም። መጨረሻውን ግን አልነገራቹኝም አርቲስት የኔነሽ ከባሏ እናት ጋር ታረቁ? ሁለት ቀን እንቅልፍ እንዴት እንደነሳኝ ብታይ ሃሃሃሃሃሃሃ ሶልን ስጠይቀው ተቆጣኝ.... ''ለምን ከፈለገች ጆሯቸውን ቆርጣ ለውሻ አትሰጠውም!'' ብሎ አጓራብኝ ሃሃሃሃሃ እንዲህ አይነት ሃገራዊ ጉዳዮች ግድ የማይሰጡት ሰው የሆነው ከመቼ ወዲህ ነው? ሃሃሃሃሃሃ ሳምሪዬ በማርያም ከዛ ጭንቅ አለም ውጪ ... ማርያምን ከፈለግሽ ተስማምተን አንድ ወር ሳትጠብቂ በ30 ደቂቃ ውስጥ አካውንትሽን ለዘለአለሙ እደልትልሻለሁ። በምንም መልኩ መመለስም አትችይም። ለማንኛውም ዳታሽን ዳውንሎድ አርጊ .... በቃ ደና ዋይ ልተኛ ነው። ስነሳ ገምተሽ ደውይ እኔ መደወል አልችልበትም ሃሃሃሃ
    9 Sep 2023

    እሪ ሃይ ረጅም ጊዜ ትላንት ድንገት አንድ ቪዲዮ ሳይ ጋኡፍ እና ሳባሌንካ ለፍፃሜ ደረሱ ይል ነበር። ትዝ አልከኝ ሚሴጁ ትዝ አለኝ። መልሼ ሳየው አሳቀኝ በራሴ ተናደድኩ ብቻ ተወው። ባጋራው ምንም ችግር የለውም ብዬ ነው። በዛውም በጋኡፍ እንኳን ደስ አለህ። እኔ ምልህ እሪ ዳታዬን ዛሬ ዳውሎድ አድርጊያለው። ፌስቡኬን ትደልትልኛለህ በዛውም ያንተ አይነት ስልክ ታጋዛኛለህ ደግሞ እንዴት እጅ እጅ እንዳለኝ ብቻ እነግርሃለው።
    8 Jun 2025
    አየህ የቀኑን ልዩነት እኔ እዛው ነበርኩ እሪ ሙት ሰልችቶኛል

    ReplyDelete
    Replies
    1. ሳምሪዬ በስማብ እንዴት ነሽ ባያሌው... ረጅም ጊዜ መሆኑ የታወቀኝ አሁን በዚ ሰዓት ስልክሽን ስመታው እምቢ ሲለኝ ስልክ ቀይራ ይሆን እንዴ? ብዬ ሳስብ ነው። እጅግ እጅግ ደክሞኝ ወደ እንቅልፍ እየሄድኩ ስለሆነ ነው ያየሁት እንጂ ለኮመንቱ ለሚሴጁ ለሚሴጄ መልሴ ልቦለድ ነበር። ካየሺው አይቼዋለሁ ለማለት እንጂ ስነሳ ስልክሽ ከሰራም ደዋይ ነኝ ካልሰራም ሌላ ሰውም ጋር ብታስደውይኝም እደርስብሻለሁ ሃሃሃሃ ስገደድ እንጂ ለሰላምታ አልደውልም ያው እንደምታውቁኝ ነኝ ሃሃሃሃ በዛውም ትመክሪኛለሽ ሳምሪነት የውነቴን ነው ወቀሳ በዝቶብኛል።

      Delete

ሱስ ነክ ጉዳዮች

Advertisement